ከ4 ወራት በፊት ባለቤቱ በሞት የተለየበት ታማኝ ውሻ እስከአሁን ድረስ ከሆስፒታሉ በራፍ አልተንቀሳቀሰም

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ4 ወራት በፊት ባለቤቱ በህመም ምክንያት በሞት የተለየበት ታማኝ ውሻ እስከአሁን ድረስ ከሆስፒታሉ በራፍ ባለ መንቀሳቀሱ የአለም መገናኛ ብዙሃን መወያያ ርእስ ሆነዋል።

የውሻው ባለቤት በጠና በመታመሙ ምክንያት ነበር ከሚኖርበት አከባቢ ወደ ብራዚል ሳኦ ፓሎ ሆስፒታል በአንቡላንስ የተወሰደው።

በዚህም ውሻው ይህ ሲያውቅ የአንቡላንሱን መንገድ በሩጫ ተከትሎ ሆስፒታሉ ድረስ መምጣቱ ሰራተኞች ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ የ59 አመት እድሜ የውሻው ባለቤት ህመሙ ከባድ ስለነበር የህክምና እርዳታ ሲያገኝበት ከነበረ ሆስፒታል ሳይወጣ ከአራት ወራት በፊት ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ውሻው ግን ይህን አላምን በማለቱ ለባለቤቱ ጤና እየተመኘ እስከአሁን ድረስ ከሆስፒታሉ በራፍ ሳይንቀሳቀስ ባለቤቱ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ነው ተብሏል።

 

 

 

ምንጭ፦www.odditycentral.com