"ሚስቶቻችሁን ቅጡ" በማለት የተናገሩት የኡጋንዳ የፓርላማ አባል ውግዘት እያስተናገዱ ነው

አንድ የኡጋንዳ ፓርላማ አባል "ሚስቶቻችሁን ቅጡ" በማለት መናገራቸው ገሪቱ ቁጣን የቀሰሰቀሰ ሲሆን÷ ግለሰቡ ከማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ውግዘትን እያስተናገዱ ነው።

የመብት ተሟጋቾች የፓርላማ አባሉ “የአዕምሮ ህክምናን ሊከታተሉ ይገባል” እስከማለት ደርሰዋል።

የፓርላማ አባሉ በይፋ ሴቶችንና በተለይም ከዚህ ቀደም ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች በአጠቃላይ ይቅርታ መጠየቅ ይገባቸዋል ሲሉም አንዳንድ የቤት ውስጥ ጥቃት መከላከል ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው።

የፓርላማ አባሉ ጥፊ እንጂ እስከሞት በሚያደርስ ደረጃ ድብደባ አድርሱባቸው አላልኩም ሲሉ ራሳቸውን ተከላክለዋል።

አክለውም "ከዚህ ቀደም ሚስቴ በጥፊ መታኝ ታውቃለች፤ እኔም እንዲሁ መትቻት አውቃለው" ብለዋል።

ሌሎች ባለሙያዎች ጥፊን ምን አመጣው ለመግባባት ሌሎች የተሻሉ ዘዴዎችን መጠቀም እየተቻለ የሚል ሀሳብን አንሸራሽረዋል።

የፓርላማ አባሉ ንግግር የተሰማው የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሬ ሙሴቬኒ "ሚስቶቻቸውን የሚማቱ ወንዶች አይረቤዎች ናቸው" ማለታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ቢቢሲ
ተተርጉሞ የተጫነው፦ አብረሃም ፈቀደ