ለ11 ዓመታት በስህተት የታሰረው ግለሰብ 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ተሰጠው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ ኬንታኪይ ግዛት ውስት በሰው መግደል ወንጀል በስህተት እስር ተፈርዶበት ለ11 ዓመታት ታስሮ የቆየው ግለሰብ 7 ነጥብ 5 ሚለየን የአሜሪካ ዶላር መስጠቱን የሉውቪል ከተማ አስታወቀ።

የ55 ዓመቱ ኬሪይ ፖርተር ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ "1 ዶላርም ይሁን 1 ትሪሊየን ዶላር፤ ያለፉ ጊዜዎችን መመለስ አይቻላቸውም" ብሏል።

ፖርተር እንደ አውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር በ1996 ነው 60 ዓመታት ተፈርዶበት እስር ቤት የገባው፡፡

ፖሊስ ፖርተር ገዳይ እንዳልሆነ መረጃ ከደረሰው በኋላ ድጋሚ ምርመራ አካሂዶ ነጻ መሆኑን አረጋግጦ የነበረ ሲሆን፥ አቃቤ ህግ መረጃውን አልሰጥም ብሎ መቆየቱ ተዘግቧል።

የሟች ወንድም ከፖርተር ጋር በመሆን አሁንም ትክክለኛ ወንገለኛው ያልተገኘለት የግድያ ድርጊቱ አዲስ ምርመራ እንዲካሄድበት ጥሪ አቅርበዋል።

 

 

 

 

 

 


ምንጭ፦ዩፒአይ
ተተርጉሞ የተጫነው፦ አብረሃም ፈቀደ