ስኳር ከጭነት መኪኖች ለመስረቅ ሲል የትራፊክ ፍሰትን ያስተጓጎለው ዝሆን

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በታይላንድ በሚገኝ አንድ አውራ ጎዳና ላይ ሰሙኑን ስኳር ከጭነት መኪኖች ለመስረቅ ሲል የትራፊክ መጨናነቅን ተመለከተ ቪዲዮን ብዙዎች በኦንላይን ተቀባብለዋል።

ምስሉ ዝሆኑ ስኳር ጭነው ከሚያልፉ የጭነት ተሽከርካሪዎች መንገድ ዘግቶ ስኳር ሲመነትፍ የሚያሳይ ነው።

የአይን ምስክሮች እንደሚሉትም ዝሆኑ በሁለት ሰዓት ውስጥ ብቻ ቢያነስ ከ12 ተሽከርካሪዎች ስኳር ሲሰርቅ ነበር።

ከሁሉም በላይ ደግሞ ዝሆኑ በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ ወደእሱ ለመጠጋትም ሆነ ወደ ጫካው ለመመለስ የሚችል ደፋር ሰው አልነበረም ነው የተባለው።

የጭነት ተሽከርካሪዎቹ በቀስታ መጓዛቸው ለስርቆቱ እንዳመቸውም ተነግሯል።

በካሆ አንግ ረዩ ናይ ተራሮች የዱር ዝሆኖች እንክብካቤ ኃላፊ ኮቪት እንደተናገሩት፥ በአካባቢው የሚገኙ ዝሆኖች ሰው አይጎዱም። የአሁኑ ሁነትም ምግብ ከመፈለግ የተነሳ ብቻም ይሆናል ነው ያሉት።

ይሁን እንጂ በወቅቱ ያጋጠመ በርካታ ተሽከርካሪዎችን በማስቆም ስኳር የመንጠቅ ተግባር ያልተለመደ አጋጣሚ እንደሆነ ነው የተገለፀው።

ምንጭ፦www.upi.com/Odd_News