የብሪታኒያ የጥንት ዘመን ነዋሪዎች ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ነበራቸው- ተመራማሪዎች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብሪታኒያ ውስጥ የተገኘ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ ቅሪተ አካል በጥንት ዘመን የአካባቢው ነዋሪዎች ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለምና ሰማያዊ አይን እንደነበራቸው እንደሚጠቁም ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።

የለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ እና የብሪቲሽ ሙዝዬም ተመራማሪዎች፥ ከ10 ሺህ ዓመት በፊት በብሪታንያ እና አካባቢዋ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ምን አይነት ኑሮ ይኖሩ እንደነበረ

ለመለየት የዘረመል ምርመራ እና የ3D ቴክኖሎጂን በመጠቀም በቅሪተ አካሎች ላይ መርመራ አካሂደዋል።

ለዚህም “ቼዳር ማን” በመባል የሚታወቀው እና እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1903 የተገኘው ቅሪተ አካል ምርምር ሲያካሂዱ ቆይተዋል።

ባካሄዱት ጥናትም፥ የወንድ ቅሪተ አካል የሆነው “ቼዳር ማን” ጥቁር የሰውነት ቆዳ፣ ሰማያዊ የአይን ቀለም እና ጥቁር የተጠቀለለ ፀጉር የነበረው መሆኑንም መለየታቸውን ተመራማሪዎቹ አስታውቀዋል።

“ቼዳር ማን” ዘረመል ከራስ ቅሉ የተወሰደ መሆኑን ያስታወቁት ተመራማሪዎቹ፤ ሌሎች አካላዊ መረጃዎቹ ደግሞ በበራሄው ዙሪያ ዳታዎችን በማሰባሰብ የተለየ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የብሪትሽ ሙዝዬም ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ክሪስ ስትሪንጀር፥ “ቼዳር ማን” ቅሪተ አካል ላይ ከ40 ዓመት በፊት ነበር ጥናት ማካሄድ የተጀመረው፤ ስለ ቼዳር ማን ሙሉ መረጃ እናገኛለን ብለን አስበን ግን አናውቅም” ብለዋል።

ምንጭ፦ www.aljazeera.com