የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የመታሰቢያ ሀውልት ተመርቋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ)ደብረታቦር ዩኒቨርስቲ ከደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ያሰራው የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የመታሰቢያ ሀውልት ትናንት ተመርቋል።

በምርቃት ስነ-ስርአቱ ከፍተኛ የክልልና የዞኑ አመራሮች እንዲሁም የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል ነው የተባለው።

የመታሰቢያ ሀውልቱ በሁለት ሚሊዮን ብር ወጭ የተገነባ ሲሆን፥ 7 ነጥብ 5 ሜትር ርዝመት እንዳለውም የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝም፣ ወጣቶች እና ስፖርት ፅህፈት ቤት ገልጿል።

 27655240_2127758567461464_5403443434717802678_n.jpg

መረጃው ከብአዴን ፅህፈት ቤት ያገኘነው ነው