የ81 ዓመቷ አዛውንት ከቻይና ቲያንጂን ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ81 ዓመቷ አዛውንት ከቻይና ቲያንጂን ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አጠናቀው መመረቃቸው ተነግሯል።

ዡዌ ሚንዡ የተባሉት አዛውንቷ ማለፍ የሚጠበቅባቸውን የኮምፒውተር ፈተና ለ6ኛ ጊዜ ከወሰዱ በኋላ ነው ለምርቃት የበቁት ተብሏል።

ዡዌ ሚንዡ ይናገራሉ፥ “እንደ እኔ ሀሳብ የህይወት ትርጉም ሁሌም ከራስ ጋር መፎካከር እና ራስን ማሻሻል ነው፤ ለዚህ ደግሞ ህልሜ እውን እንዲሆን ይህንን እድል ለሰጠኝ ቲያንጂን ዩኒቨርሲቲ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለው”።

“ለእኔ በህይወቴ ውስጥ በጣም ወሳኙ ነገር ኑሮን በምፈልገው መንገድ መኖሬ ነው” ሲሉም በምርቃ ስነ ስርዓታቸው ላይ ተናግረዋል።

ziwe.jpg

ዡዌ ሚንዡ ትምህርታቸውን በኢ ኮመርስ ነው ያጠናቀቀቁት።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2014 በርቀት ትምህረት መርሃ ግብር መማር የጀመሩት ዡዌ ሚንዡ፥ በወቅቱ እድሜያቸው 77 ነበር።

ዡዌ ሚንዡ ትምህርታቸውን በተከታተሉበት 4 ዓመታት ጊዜ ውስጥ በቤታቸው የሚገኘው ቴሌቪዥን አንድም ጊዜ ተከፍቶ እንደማያውቅ ይናገራሉ።

ምክንያቱ ደግሞ ቴሌቪዥን ለማየት የሚባክነውን ሰዓት ለጥናት ማዋል በማሰብ እንደሆነ ነው ዡዌ የተናገሩት።

ለመጨረሻ መመረቂያ ፈተናቸውን ለማለፍን ለስድስት ተከታታይ ጊዜ ፈተና ወስደው በመጨረሻም አሳክተዋል ነው የተባለው።

ዡዌ ሚንዡ አምስት ቋንቋዎችን አቀላጥፈው ያውቃሉ የተባለ ሲሆን፥ ቋንቋዎቹም ቻይንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዘኛ፤ የሩሲያ እና ላቲን ናቸው።

ምንጭ፦ www.thestar.com