ከ98 በመቶ በላይ የሰውነታቸውን ክፍል የተነቀሱት የ69 ዓመቷ አዛውንት

 አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ69 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ የሆኑት አዛውንት 98 ነጥብ 75 በመቶ የሰውነት ክፍላቸው በንቅሳት በማጌጥ ስማቸውን በዓለም የድንቃድንቅ መዝገቦች ላይ አስፍረዋል።

ቻርሎቴ ጉተንበርግ የተባሉት አዛውንቷ በደቡብ ምስራቅ አሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት ነዋሪ ሲሆኑ፥ መላ ሰውነታቸው በሚባል መልኩ በተለያዩ የጥበብ ስራ በንቅሳቶች ማሸብረቃቸው ነው ለዚህ ያበቃቸው።

“የምፈልገውን እንደማገኝ አስቀድሜ አውቅ ነበር” ብለዋል ጉተንበርግ።

አዛውንቷ በአውሮፓውያኑ 2015 የሰውነታቸውን 91 ነጥብ 5 ክፍል በመነቀስ ክብረ ወሰኑን ይዘው የነበሩ ሲሆን፥ አሁን ላይም በራሳቸው የተያዘውን ክብረወሰን ነው ያሻሸሉት።

c4_tcm25-511497.jpg

አዛውቷ አሁን በመጠኑ የፊታቸው እና የእጃቸው ክፍል ካልሆነ በስተቀር ሙሉ ሰውነታቸው በንቅሳቱ ተሸፍኗል።

ይህ ብቻ አይደለም የጉተንበርግ ባለቤት ቹክ ሄልምኬም ሰውነታቸው በንቅሳት መሸፈኑ ባል እና ሚስት የብዙሃን ቀልብ ስቧል ነው የተባለው።

 

ምንጭ፦www.upi.com