በቱርክ የፅዳት ሰራተኞች የተጣሉ መጻህፍቶችን በመሰብሰብ ቤተ መጻህፍት ከፍተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቱርክ በፅዳት ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የተጣሉ መጻህፍቶችን ከቆሻሻ ውስጥ ሰብስበው ቤተ መጻህፍት መክፈታቸው ተሰምቷል።

ቤተ መጻህፍቱ ከዚህ በፊት ለብሎኬት ማምረቻነት ጥቅም ላይ ሲውል በነበረ ቤት ውስጥ የተከፈተው።

ከዚህ በፊት ወደ ቆሻሻ መጣያ ስፍራዎች ተጥለው የነበሩ መፅሃፍቶችን በመሰብሰብ የተከፈተው ቤተ መፅሃፍቱን ለማስዋብም በቆሻሻ መጣያ ስፍራዎች የወዳደቁ ቀለማት ጥቅም ላይ ውለዋል።

ቤተ መጻህፍቱ ውስጥ የሚገኙት መጻህፍቶች በጽዳት ስራ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች ለወራት በሰባሰቧቸው መጻህፍት የከፈቱት ሲሆን፥ በኋላ ላይ በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎችም መጽሃፍቶችን መለገሳቸው ተነግሯል።

ስፍራውም ካሳለፍነው ዓመት መስከረም ወር ጀምሮ ለህዝብ ክፍት መደረጉም ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅትም በቤተ መጻህፍቱ ውስጥ ልብ ወለዶችና ልብ ወለድ ያልሆኑ መጽሀፍቶች እንዲሁም ለተለያዩ ሳይንሳዊ ምርምር ስራዎች የሚውሉ መጻህፍቶችን ጨምሮ ከ6 ሺህ በላይ መጻህፍት ይገኛሉ ተብሏል።

መጻህፍቶቹም እንግሊዘኛ እና ፈረንሳይኛን ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉ ናቸው።

ምንጭ፦ www.upi.com