የጃፓን ባቡሮች እንደ ውሻ መጮህ ሊጀምሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጃፓን የባቡር ተመራማሪዎች እንስሳት ወደ ባቡር ሀዲድ እንዳይገቡ ለማባረር የሚያስችላቸውን ቴክኖሎጂ መስራታቸው እየተነገረ ነው።

አዲሱ ቴክኖሎጂያቸው የውሻ እና የአጋዘን ድምፅን የሚያስመስል ሲሆን፥ ይህም በባቡር ጉዞ ወቅት የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ ይረዳል ነው የተባለው።

የቶክዮ የባቡው ድርጅት ቴክኒካል ምርምር ክፍል በቴክኖሎጂው ላይ ባደረገው ሙከራም ስኬታማ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

የውሻ እና የአጋዘን ድምፅ የሚያወጣው ባቡሩ በየ100 ኪሎ ሜትር ርቀት በእንስሳት ላይ ይደርስ የነበረውን የመገጨት አደጋ በ45 በመቶ መቀነሱም ነው የተነገረው።

በሙከራውም የአጋዘን ድምፅ ለ3 ሰከንድ እንዲሁም የውሻን ድምፅ ደግሞ ለ20 ሰከንዶች እንዲሰማ በማድረግ ነው የተካሄደው።

ቴክኖሎጂው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በሚያዝያ ወር 2019 ስራ ላይ ይውላል ብለው እንደሚያምኑ የቴክኖሎጂው ፈጣሪዎች አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ www.upi.com