የ99 ዓመቷ አዛውንት የአካል ብቃት አስተማሪነታቸውን ባለማቋረጥ ስማቸውን በድንቃድንቅ መዝገብ አሰፈሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) እድሜ ሳይገድባቸው የአካል ብቃት እንቅሰቃሴዎችን በማስተማር ላይ ያሉት የ99 ዓመቷ አዛውንት “በትልቅ እድሜ የዮጋ ስፖርትን የሚያሰለጥኑ” በሚል ስማቸውን በዓለም የድንቃድንቅ መዝገቦች ላይ አስፍረዋል።

የ99 ዓመቷ ታኦ ፖርቾን-ሊንች በአሁኑ ጊዜ ኒው ዮርክ ውስጥ በቤት ውስጥ ዮጋን ጨምር በአካል ብቃት እንቅሰቃሴ መምህርነት ስራ መቀጠላቸው ነው በድንዳድንቅ መዝገብ ስማቸውን ለማስፈር ያበቃቸው ተብሏል።

እኝህ አዛውንት አሁን ለክብር ያበቃቸውን የቤት ውስጥ የዳንስ ስፖርቶች መምህርነት ሴቶች ብዙም የማይደፍሩትን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በፍላጎታቸው መስራት በመጀመራቸው ነው።

በ85 ዓመታቸው ይበልጥ ለመሥራት ከተነሳሱ በኋላ እስከ ዛሬ ድረስ በስፖርት ውስጥ ሰባት ጊዜ በአንደኛነት ድል ተቀዳጅተዋል ነው የተባለው።

sjsf_tcm25-506411.jpg

አዛውንቷ የዜን እና ዊምሲካል የስፓርት የሥነ ጥበብ ክፍል የህይወት ልምዳቸው ለዚህ ስኬት እንዳበቃቸውም ይነገራል።

ታኦ ስለ ህይወት ልምዳቸው ሲጠየቁ "ጠዋት ላይ ከእንቅልፍ ከተነሳሁ በሕይወቴ ውስጥ ከሁሉ የተሻለ ቀን እንደሚሆን እናገራለሁ” ብለዋል።

በዚህም በአዕምሮ ውስጥ የሚቀመጡት ነገሮች ሁሉ ትክክለኛ መሆናቸውን አምናለሁ ነው ያሉት።

ምንጭ፦ guinnessworldrecords.com