መኪናውን የት እንዳቆመ የረሳው ግለሰብ ከ20 ዓመት በኋላ አግኝቶታል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጀርመኗ ፍራንክፈትር ነዋሪ የሆኑት ግለሰብ ተሽከርካሪያቸው መጥፋቱን ለፖሊስ ሪፖርት ካደረጉ ከ20 ዓመት በኋላ አግኝተዋል።

ጀርመናዊው ግለሰብ ተሽከርካሪያቸውን የት ቦታ እንዳቆሙ በመርሳታቸው ነበር ጠፍቶብኛል በሚል ለፖሊስ አምልክተው የነበረው።

በዚህ ሳምንት ግን ግለሰቡ ከ20 ዓመት በፊት ከተለያዩት ተሽከርካሪያቸው ጋር ዳግም መገናኘታቸው ነው የተነገረው።

ግለሰቡ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1997 ነበር ተሽከርካሪው እንደጠፋበት ለጀርመን ፍራንክፈርት ፖሊስ ያመለከተው።

የከተማው የፖሊስ ባለስልጣናትም ተሽከርካሪውን ማግኘታቸውን ያስታወቁ ሲሆን፥ መጥፋቱ ሪፖርት የተደረገለት ተሽከርካሪ እንዳልተሰረቀና በድሮ የኢንዱስትሪ ህንፃ ጊቢ ውስጥ ቆሞ እንደተገኘ አስታውቀዋል።

ተሽከርካሪው ሊገኝ የቻለውም ህንፃው ሊፈርስ መሆኑን ተከትሎ በአካባቢው ያሉ ንብረቶች ከቦታው እንዲነሱ ሲደረግ ነው።

በመጨረሻም የ76 ዓመቱ አዛውንት ከሴት ልጃቸው ጋር በመሆን ከ20 ዓመት በፊት ከተለያዩት ተሽከርካሪያቸው ጋር ዳግም ተገናኝተዋል ነው የተባለው።

ሆኖም ግን ተሽከርካሪው ረጅም ዓመት ከሞቆም ጋር በተያያዘ የማርጀት እና የማበላሸት አደጋ ስላጋጠመው ዳግም መነዳት አይችልም።

ምንጭ፦ www.irishtimes.com