ሚስቱ በህልሟ ያየቻቸውን የሎተሪ ቁጥሮች ቆርጦ 100 ሺህ ዶላር ያሸነፈው ግለሰብ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ሚስቱ በህልሟ ያየቻቸውን የሎተሪ ቁጥሮች ቆርጦ 100 ሺህ ዶላር ያሸነፈው ባል ልዩ እድለኛነት አስግራሚ ሆኗል።

ፍሬድሪክ ኖክስ ይባላል፤ በቨርጂኒያ የመሚኖረው ባለ ዕድል ሚስቱ በህልሟ ባየቻቸው ቁጥሮች መሰረት ባለ 5 ረድፍ ቁጥር ትኬት ለመቁረጥ ይወስናል።

በዚህም መሰረት ሚስቱ በህልሟ 1-8-14-20-31 የሚሉ ተከታታይ የእድል ቁጥሮችን በማየቷ ይህን ቁጥር ቆርጦ እድሉን መጠባበቅ ጀመረ።

ጊዜው ደርሶ የሎተሪው እጣ ሲወጣ ሚስት በህልሟ ያየችው ቁጥር አሸናፊ ቁጥር ሲሆን፥ በጣም መገረሟን ነው ኖክስ የተናገረው።

በህልሟ ያየችውን የሎተሪ እጣ ቁጥር ደጋግማ እየተመለከተች እድለኛ መሆኑን ለማመን እንደከበዳት ገልጿል።

ምንጭ፦ዩናይትድ ፕረስ ኢንተርናሽናል