ካሊፎርኒያዊው ጎልማሳ በልደት ቀኑ 750 ሺህ ዶላር የሎተሪ ሽልማት አሸንፏል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ውስጥ የሚኖረው ጎልማሳ በልደት ቀኑ 750 ሺህ አሜሪካ ዶላር የሎተሪ ሽልማት እድለኛ ሆኗል።

ሄስተን ሁፍስ ይባላል፤ የ35ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ባከበረበት ማግስት የሚፋቅ የሎተሪ ቲኬት በ10 ዶላር ይገዛል።

በፋቀው የሎተሪው የእጣ ቁጥርም የ750 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በተሸላሚ መሆኑን ያውቃል።

ሎተሪው ፊደላትን በመገጣጠም የእድል እጣ የሚያስገኝ አሰራር ያለው ሲሆን፥ ሁፍስ የፊደል አቆጣጠርን እንደ አዲስ ለመለማመድ ፈልጌ ነበር ሎተሪውን ገዛሁት ይላል።

በዚህም ያልጠበቅኩትን ገንዘብ ሽልማት አሸነፍኩ ሲል በቀልድና በደስታ ተናግሯል።

በልደት ቀኑ ከተሰጣቸው ስጦታዎች በመጨረሻ ጊዜ የተሰጠውም 750 ሺህ ዶላር የሚያስገኘው ነው።

በገንዘቡ ጠቃሚ ስራዎችን ለመስራት ማቀዱን ተናግሯል።

ምንጭ፦ ዩናይትድ ፕሬስ ኢንተርናሽናል