በ2 ጎማ ብቻ መኪናቸውን የሚያሽከረክሩት እንግሊዛውያን ወንድማማቾች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) እንግሊዛውያኑ ወንድማማቾች ተሽከርካሪያቸውን በሁለት ጎማ ብቻ በማሽከርከር እና በአስገራሚ አፓርኪንግ ችሎታቸው የበርካቶችን ቀልብ ስበዋል።

አሊስታር ሞፋት እና ወንድሙ ከዚህም አልፈው በዚህ ተግባራቸው ስማቸውን የዓለም የድንቃ ድንቅ እና የከብረወሰኖች መዝገብ ላይ ማስፈር ችለዋል ነው የተባለው።

ሁለቱ ወንድማማቾች በጣም ተቀራርበው ሁለት ተሽከርካሪዎችን በሁለት ጎማ ብቻ ማሽከርከር በሚል ነው ስማቸውን በዓለም የድንቃድንቅ እና የከብረ ወሰኖች መዝገብ ላይ ማስፈር የቻሉት።

በዚህም ከዚህ ቀደም ሃን ዩዌ እና ባዎ በተባሉ ቻይናውያን ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በእጃቸው አስገብተዋል።

ተግባሩ በጣም አደገኛ እና ከባድ በመሆን የሚናገሩት አሊስታር እና ወንድሙ፥ በዚህ ስራ ላይ ስኬትህም ውድቀትህም በአንድ ቀን ነው ሊመጣ የሚችለው ብለዋል።

ምንጭ፦ www.guinnessworldrecords.com