የባለቤታቸውን ጭቅጭቅ በመሰለቸት 10 ዓመት በጫካ ተደብቀው ለመኖር የተገደዱት አዛውንት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) አንድ አትክልተኛ አዛውንት ከባለቤታቸው ጋር የሚፈጠረውን ተደጋጋሚ ጭቅጭቅ በመሰልቸቱ ቤታቸውን ጥለው በዱር ውስጥ ለ10 ዓመታት ለመኖር ተገደዋል።

በበርኒንግሃም ነዋሪ የሆኑት የ62 ዓመቱ አዛውንት ማልኮልም አፕለጋቴ፥ ግንኙነታቸው ወደ ከፋ ሁኔታ ከመድረሱ በፊት ከባለቤቱ ጋር ለሶስት ዓመት ኖረዋል።

“ለሦስት ዓመታት ያህል ከባለቤቴ ጋር አብረን ኖረናል፤ በዚህም እርስ በርሳችን በመተጋገዝ እንኖር ነበር” ሲሉ እኝህ አዛውንት ተናግሯል።

ጭቅጭቁ የተጀመረው “ብዙ ጊዜ በአትክልት ስፍራ ከምታሳልፍ ለምን አብረን ብዙ ጊዜ አናሳልፍም” ከሚል ነው።

በዚህ ምክንያት በጣም ብዙ ክርክሮች የተፈጠሩ ሲሆን አፕለጋቴ ይህ ሁኔታ አልጣማቸውም።

ስለሆነም የሥራ ሰዓታቸውን በመጨመራቸው ምክንያት ከባለቤታቸው ቁጣን ያስተናግዳሉ።

በዚህም ምክንያት ባለቤታቸውን ትተው በድብቅ በኪንግስተን አቅራቢያ በደቡብ ምዕራብ ለንደን ወደሚገኘው ጥቅጥቅ ያለ ደን ውስጥ በመግባት መኖር ጀመሩ።

በዚህ ደን እንደሚኖሩ ማንም ሰው አያውቅም ነበር።

በዚህ ጫካ 10 ዓመታትን ያሳለፉት ማልኮልም፥ ከእህታቸው ጋር የነበራቸውን ግንኙነት አቋርጠው እንደነበርም ገልፀዋል።

በዚህም እህታቸው ማልኮልም ሙቷል በሚል ተስፋ ቆርጣ እንደነበር ተናግረዋል።

ከ10 ዓመታት በኋላ ወደ ግሪንዊች የተባለ ታሪካዊ ሰፈር ሲገቡ ለእህታቸው አንድ ደብዳቤ እንደፃፉላት እና እሷም ስልክ እንደደወለችላቸው ነው የጠቀሱት።

ማልኮልም በአሁኑ ወቅት በግሪንዊች ለቤት አልባ ሰዎች የሚሰጥ መጠለያ ለእርሳቸውም ተሰጥቷቸው በዚያ ማእከል እየኖሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቀድሞ ባለቤታቸውን እንኳን ቢያጡ የሚወዱትን የአትክልተኝነት ሙያ ግን አሁንም እንደሚቀጥሉ ነው የገለፁት።

 

 

 

መንጭ፦nzherald.co.nz