አመታዊው ሚስትን ተሸክሞ የመሮጥ ውድድር በአሜሪካ ተካሂዷል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 30 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የሚካሄደው አመታዊው ሚስትን ተሸክሞ የመሮጥ ውድድር በአነስተኛዋ የኒውሪ መንደር ተካሂዷል።

ውድድሩ ባሎች ሚስቶቻቸውን በትክሻቸውና በጀርባቸው በመሸከም የሚያደርጉት ሩጫ ነው።

በዚህም የተደረደሩ እንጨቶችን እና ያዝ በሚያደርግ አነስተኛ ውሃ ውስጥ በመዝለልና በመራመድ ሚስቶቻቸውን እንደተሸከሙ መሮጥ ይጠበቅባቸዋል።

ከዚህ ባለፈም ሌሎች አነስተኛ መሰናክሎቸን ማለፍም የውድድሩ አንድ አካል ነው።

በዚህ ውድድር ታዲያ ከቨርጅኒያ ሌክሲንግተን የመጡት ጃክ እና ክርስተን በርኔይ የተሰኙት ጥንዶች የዘንድሮው ውድድር አሸናፊ ሆነዋል።

ጥንዶቹ 12 ሳጥን ቢራን ጨምሮ እስከ 630 የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

አሸናፊ መሆናቸውን ተከትሎም አሜሪካን በመወከል በፊንላንድ በሚካሄደው አለም አቀፍ ውድድር ላይ የሚሳተፉ ይሆናል።

 

 

ምንጭ፦ ዩናይትድ ፕረስ ኢንተርናሽናል