በቻይና በሰውና በበሬ መካከል የሚደረገው ነፃ ትግል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምስራቃዊ ቻይና አንድ ባህላዊ ስፖርታዊ ውድድር አለ፤ ይህም ሰዎች ከበሬ ጋር የሚደርጉት ነፃ ትግል ነው።

ይህ የባህል ስፖርታዊ ውድድር በዘንድሮው ዓመትም በምስራቃዊ ቻይና ዤጂያንግ ግዛት ጀያዢንግ ከተማ የተካሄደ ሲሆን፥ በርካቶችም ውድድሩን ተመልክተዋል ነው የተባለው።

bull_fight_china_3.jpg

ከበሬ ጋር የሚደረገው የነፃ ትግል “ጉዋኒዩ” የሚል መጠሪያ ያለው ሲሆን፥ ሁዊ በተባሉ ህዝቦች ነው በብዛት የሚዘወተረው።

የጀያዢንግ ታሪክ እንደሚያሳየው ከሆነ “ጉዋኒዩ” የተባለው ባህላዊ ስፖርት የተጀመረው በዩዋን እና ሶንግ ስርወ መንግስ ዘመን ነው።

bull_fight_china_2.jpg

በውድድሩ ላይ የሚካፈሉት የሁዊ ህዝቦች ያለ ምንም መሳሪያ እጃቸውን ባዶ ነው ከበሬው ጋር ነፃ ትግል የሚገጥሙት ተብሏል።

bull_fight_china_4.jpg

ይህ ባህላዊ ስፖርት በርካታ ሰዎች የሚታደሙበት መሆኑም ተነግሯል።

ምንጭ፦ Peoples Daily China