አሜሪካዊው ታዋቂ የካንትሪ ሙዚቃ አቀንቃኝ ዶን ዊሊያስም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካዊው የካንትሪ (ሀገረ ሰብ) ሙዚቃ አቀንቃኝ ዶን ዊሊያምስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ዶን ዊሊያምስ መጠነኛ ህመም ካጋጠመው በኋላ በ78 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱም ተነግሯል።

ዶን ዊሊያምስ የሙዚቃ ህይወቱን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1971 የጀመረ ሲሆን፥ 17 ቁጥር አንድ የተባሉ የሀገረ ሰብ (ካንትሪ) የሙዚቃ አልበሞችን አድማጮች ዘንድ በማድረስ ተዋቂነትን አትርፎበታል።

በዚህም የካንትሪ (ሀገረ ሰብ) ሙዚቃ ታላቁ ሰው የሚል ክብርን አስከመቀዳጀት ደርሷል።

በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ ከሆኑ የዶን ዊሊያምስ ሙዚቃዎች ውስጥም “ዩ አር ማይ ቤስት ፍሬንድ፣ አይ ብሊቭ ኢን ዩ እና ሎርድ አይ ሆፕ ዚስ ዴይ ኢስ ጉድ” የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው።

በተያያዘ ዜና ሌላኛው አሜሪካዊ ታዋቂ የሀገረሰብ (ካንትሪ) ሙዚቃ አቀንቃኝ ትሮይ ጄንትሪ እለት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

ትሮይ ጄንትሪ በትናንትናው እለት ባጋጠመው የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋ በተወለደ በ50 ዓመቱ ህይወቱ ማለፉም ተነግሯል።

Troy_Gentry.jpg

ታዋቂው የሀገረሰብ (ካንትሪ) ሙዚቃ አቀንቃኝ ትሮይ ጄንትሪ ድንገተኛ ሞት ዜናም በርካታ ወዳጆቹን እና አድናቂዎቹን ያስደነገጠ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ