የእጇን ጥፍር ከ5 ሜትር በላይ ያሳደገችው አሜሪካዊት በዓለም የድንቃድንቅ መዝገቦች ላይ ስሟን አስፍራለች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2009(ኤፍ ቢ ሲ) የእጇን ጥፍር ከ5 ሜትር በላይ ያሳደገችው አሜሪካዊት በዓለም የድንቃድንቅ መዝገቦች ላይ ስሟን አስፍራለች

የእጅ ጥፍር መርዘም ሲተኙ ሊሰበር እንደሚችል፣ ለስራ አመቺ እንዳልሆነ ቢታሰብም የቴክሳሷ ሰው ግን ይህ አስተሳሰብ እኔ ዘንድ የለም ትላለች።

አያና ዊሊያምስ በሂውስተን ከተማ ነዋሪ ነች።

በዓለም የድንቃድንቅ መዝገቦች በ63ኛው የ2018 እትም ላይ ስማቸው ከሰፈሩ ሰዎችም አንዷ ሆናለች።

ዊሊያምስ ላለፉት 23 ዓመታት ጥፍሯን ለማሳደግ በሰራችው ስራ 5 ሜትር ከ76 ሳንቲ ሜትር የሚረዝም ጥፍር ባለቤት ሆናለች።

በዚም ባለረዣዥም ጥፍር ባለቤት ውድድርም ቀዳሚዋ በመሆን ነው በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስሟ የሰፈረው።

ዊሊያምስ ለእያንዳንዱ ጥፍሮቿ የራሳቸውን ውበት በመስጠትና ቀለም በመቀባትም ጥፍር አሳማሪነቷ የብዙዎችን ቀልብ ስባለች።

ታዲያ ጥፍሮቿን ለማሳመር ቢያንሰ አንድ ሳምንት ይወስድባታል።

ጥፍሮቿ ውብና ንፁህ እንዲሆኑና እንዳይሰባበሩ የተለያዩ ማፅጃዎችንና ማጠንከሪያዎችን ትጠቀማለች።

ዊሊያምስ በረጅም ጥፍሮቿ ስሟ ከሂውስተን አልፎ በዓለም ላይ እንዲታወቅ ማድረግ ሳይሆን ልጆቿ የሚፈልጉትን ነገርና የያዙትን ዓላማ ማሳካት እንደሚችሉ ማስተማር መሆኑ ደግሞ ለብዙዎች ትምህርት ሆኗል።

ጥፍሯን ስታሳድግ ትዕግስት፣ ፅናት፣ ብርታትና ተነሳሽነት ግቧን ለማሳካት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ማወቋን ለልጆቿ የያዙትን ዓላማ ከዳር ለማድረስ ሊጠቀሙባቸው እንደሚገባ እያስተማረች መሆኗንም ተናግራለች።

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፦www.allure.com