የዓለም የፂም ውድድር በአሜሪካዋ ቴክሳስ ተካሂዷል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለማችን ምርጥ እና ለየት ያለ ፂም ያላቸው ሰዎች ውድድር በአሜሪካዋ ቴክሳስ ተካሂዷል።

በሺህ የሚቀጠሩ ግለሰቦችም የተለያየ የፂም አበቃቀል እና ቅርፅ ይዘው ባሳለፍነው እሱድ በአሜሪካዋ ቴክሳስ አውስቲን በተካሄደው የ2017 የፂም ውድድር ላይ ተገኝተዋል።

በውድድሩ ላይ በፂሙ ፊቱን ከውሻ ፊት ጋር ከማሳሰለው ጀምሮ በርካታ ለየት ያለ ጺም ይዘው የቀረቡ ሰዎችም የአሸናፊነት ዝርዝር ውስጥ ገብተዋል።

bread_2.jpg

የፊት ፂሙን በሚያምር መልኩ ይዞ ቀርቧል በሚል ጄሰን ኪሌይ የውድድሩን አሸናፊተን ተቀዳጅቷል።

በተፈጥሮ ዘርፍ ደግሞ ሚካኤል ዎሊንበ 60 ሴንቲሜትር በሚረዝመው ፂሙ አሸናፊ የሆነ ሲሆን፥ የተለያየ ቅርጻ ቅርጽ ይዘው የተገኙ በርካታ ግለሰቦችም ውደድሩ ላይ

ተሸላሚ ሆነዋል።

bread_3.jpg

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk