በህንድ የምትገኘው ትንሽ መንደር በንፅህናዋ ለዓለም አርዓያ ሆናለች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ በሚገኙ ከተሞች የቆሻሻ ክምሮችን በየመንገዱ ማየት የተለመደ ነው፡፡

ሆኖም በሀገሪቱ ሜጋላያ ክልል የምትገኘው የማውሊኖንግ መንደር ግን ፍፁም ንፁህ በመሆን ለቀሪው ህንድና ለመላው ዓለም ተምሳሌት ሆናለች፡፡

asian_village.jpg

በመንደሯ የሚኖሩ ሰዎች ለቆሻሻ ምንም ዓይነት ትዕግስት የላቸውም፤ በእያንዳንዱ የመንገድ ዳርቻዎች የሚያገኟትን ቆሻሻ በተወሰነ ስኩዌር ሜትር ርቀት ባስቀመጡት ቅርጫት ያስቀምጣሉ፡፡

wow_village.jpg

600 ሰዎች በሚኖሩባት በዚህች መንደር ከቱሪስቶች በስተቀር ከፕላስቲክ የተሰሩ እቃዎችን መጠቀም የማይቻሉ ሲሆን ማጨስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡

ይህች መንደር በንፅህና አጠባበቋ ለመጀመሪያ ጊዜ የመገናኛ ብዙሃንን ቀልብ የሳበችው በ2003 ሲሆን ከህጻናት እስከ አዛውንት ቆሻሻን ማፅዳት የየዕለት ልምዳቸው ነው፡፡

የማውሊኖንግ ህጻናት ዘወትር ማለዳ ወደ ትምህርት ቤት ከመሄዳቸው በፊት መጥረጊያና ቅርጫታቸውን በመያዝ በአካባቢያቸው የወዳደቁትን ቆሻሻዎች እያነሱ ያፀዳሉ።

maxresdefault.jpg

ከታላላቆቻቸው ጋር በመሆንም ደረቅ ቆሻሻዎችን በመለያየት የሚቃጠሉትን ለብቻ በማድረግ ያቃጥላሉ፤ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ለብቻ ይሰብስባሉ፡፡

የዛፍ ቅጠላቅጠሎችን ደግሞ በጉድጓድ ውስጥ በመቅበር ለሰብል ማዳበሪያነት ያውሏቸዋል፡፡

በዚህ የዘወትር ተግባሯ ማውሊኖንግ በሀገረ ህንድ በቆሻሻ የሚታወቁ በርካታ መንደሮችን አንገት አስደፍታለች።

111.jpg

በመንደሯ ከቆሻሻ ጋር የተያያዙ በሽታዎች ድርሽ ብለው አያውቁም ነው የተባለው፡፡

የማውሊኖንግ መንደር በዋናነት የፀሐይ ሃይል ተጠቃሚ ስትሆን የአበባና አትክልት ተንከባካቢ እንዲሁም የመንገድ ዳር የሚያስውቡ ሰራተኞች አሏት፡፡

ምንጭ፡- www.odditycentral.com