ቱርካዊው ግለሰብ 16 የሲሚንቶ ሙሊቶችን ከ5 ሰከንድ በታች በሆነ ጊዜ ደረቱ ላይ አስፈልጧል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 4 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርካዊው የማርሻል አርት ስፖርተኛ አዲስ ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ችሏል።

አሊ ባህቼቴፕ ደረቱ ላይ 16 የሲሚንቶ ሙሊቶችን በማስፈለጥ ነው አዲስ ክብረ ወሰን ማስመዝገብ የቻለው።

በዚህም ስሙን በአለም የድንቃ ድንቅ መዝገቦች (ጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ) አስፍሯል።

ግለሰቡ ሙሊቶችን ለማስፈለጥም 4 ነጥብ 75 ሰከንድ ጊዜ ወስዶበታል።

ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ መጠን ያላቸውን የሲሚንቶ ሙሊቶች ለማስፈለጥ በ6 ነጥብ 33 ሰከንዶች ጊዜ ወስዶበት ነበር።

ይህም የቀደመውን የራሱን ክብረ ወሰን ከ1 ሰከንድ በላይ በሆነ ጊዜ ማሻሻል አስችሎታል።

ግለሰቡ በጀርባው በመተኛት 16ቱን የሲሚንቶ ሙሊቶች ሆዱ ላይ በማስደርደር ነበር ያስፈለጠው።


ምንጭ፦ www.upi.com