ኤሌክትሪክ ተመጋቢው ህንዳዊ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መኖሪያው ሰሜናዊ ህንድ በምትገኘው ሙዛፋራንጋር የሆነው ናሬሽ ኩማር “ተፈጥሮ ለየት ያለ ነገር ለግሳኛለች” ይላል።

ከፍተኛ ቮልቴጅ ያለው ኤሌክትሪክ በባዶ እጁ በሚነካበት ጊዜ የማይዘው ናሬሽ ከዚህም የተለየ ነገር አደርጋለው ሲል ተሰምቷል።

ይህም ከፍተኛ ቮልቴጅ ያለውን የኤሌክትሪክ ሀይል ለምግብነት ማዋሉ ነው።

የ42 ዓመቱ ናሬሽ ኤሌክትሪክ እንደማይዘው ያወቀው በድንገት ሲሆን፥ ይህም በስራ ቦታ ላይ ሽፋን የሌለው የኤሌክትሪክ ገመድ ነክቶ ምንም አለመፈጠሩን ተከትሎ ነው።

ናሬሽ በመትረፉ ፈጣሪውን አመስግኖ ከኤሌከትሪክ ከመራቅ ይልቅ የተለጣ የኤሌከትሪክ ሽቦዎችን በእጁ በመያዝ ሌሎች ሙከራዎችን ማድረግ የጀመረ ሲሆን፥ በዚህ ሙከራው ነው ኤሌክትሪክን እንደ ምግብነት መጠቀም የጀመረው ተብሏል።

“በማንኛውም ሰዓት ሲርበኝ እና ቤት ውስጥ የሚበላ ምግብ ከሌለ ሀይል ያለው የኤሌክትሪክ ሽቦ ለግማሽ ሰዓት ያክል ይዤ እቆያለው፤ በዚህም ሙሉ በሙሉ የጥጋብ ስሜት ይሰማኛል” ብሏል።

“የኤሌከርክ ሀይለን ልክ እንደ ምግብ ነው የምመገበው” የሚለው ናሬሽ፥ “በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ቁሳቁሶቸን በምነካበት ጊዜ ጉዳት አያደርሱብኝም፤ ይልቁንም ውስጤ ላይ ያለውን ሀይል ለማመጣጠን ይረዱኛል” ብሏል።

በአሁኑ ጊዜም የሰውነቴ 80 በመቶ ከኤሌክትሪክ ሀይል የተሞላ እንደሆነ ይሰማኛል ሲልም ይናገራል።

“ቤት ውስጥ ምንም አይነት ማብሪያ እና ማጥፊያ የለም” የሚሉት የናሬሽ ባለቤት፥ “አንዳንዴ ልጆቻችንን ኤሌክትሪክ እንዳይዛቸው እሰጋለው” ይላሉ።

ናሬሽ ይናገራል፥ “ልዩ መሆኔን አውቃለው፤ ማንኛውም ሰው እኔ እንደማደርገው ማድረግ አይችለም፣ ሚስቴ በእኔ ተግባር ባትደሰትም በርካቶችን ግን እንደማስደምም አውቃለው” ብሏል።

ናሬሽ ምንም ሽፋን የሌላቸው እና የተላጡ የኤሌክትሪክ ሽቦዎችን በባዶ እጁ ሲይዝ እና በአፉ ሲነክስ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች በማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች ላይ በርካቶች እየተቀባበሉት ሲሆን፥ “ህይወት ያለው አምፖል” የሚል ስያሜም ሰጥተውታል።

ምንጭ፦ www.odditycentral.com