በ1 ሰዓት ከ2 ሺህ 500 በላይ ፑሽአፕ የሰራው አውስትራሊያዊ አዲስ ክብረ ወሰን ያዘ

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 6፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ52 ዓመቱ አውስትራሊያዊ በአንድ ሰዓት ከ2 ሺህ 500 በላይ ፑሽ አፕ በመስራት አዲስ የዓለም ክብረወሰን ይዟል።

ካርልተን ዊሊያምስ የተባለው አውስትራሊያዊው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2015 ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ነው ክብረወሰኑን በእጁ ያስገባው ተብሏል።

ካርልተን በ60 ደቂቃዎች ውስጥም 2 ሺህ 682 ፑሽ አፕ ስፖርትን በመስራቱም ስሙ በዓለም የድንቃድንቅ እና የክበረ ወሰኖች መዝገብ ላይ መስፈር ችሏል።

“ሙከራዬ ክብረ ወሰኑን ለማሻሻል ነበር፤ ይህንንም አሳክቻለው” ሲል ዊሊያም አስተያየቱን ሰጥቷል።

ዊሊያም ፑሽ አፑን በሚሰራበት ጊዜም እጆቹን መሬት ላይ ማድረግ ይጠበቅበት ነበር፤ በመቀጠልም ክርኖቹ 90 ዲግሪ በሚታጠፉበት ጊዜ ነው ፑሽ አፑ የሚቆጠርለት።

ክብረ ወሰኑን ባሻሻለበት ጊዜም ሰዓቱ ለእረፍት በሚል ያልተቋረጠ ቢሆንም፥ ዊሊያም ግን በመሃል እያረፈ እያረፈ እና ትንፋሽ እየወሰደ ነበር ተብሏል።

ምንጭ፦ www.upi.com/Odd