ሞሮኮ በራባት ግዙፍ ሁለገብ ትያትር ቤት እየገነባች ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 5፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሞሮኮ በዋና ከተማዋ ራባት ግዙፍ የሆነውን ሁለገብ ትያትር ቤት በመገንባት ላይ ትገኛለች።

ግንባታው በፈረንቹ 2019 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህ ትያትር ቤት ባለብዙ አገልግሎት ክፍሎች በውስጡ እንደሚዝ ነው የተጠቆመው፡፡

በውስጡ 1 ሺህ 822 ሰዎችን የሚያስተናግድ የትያትር መከወኛ አዳራሽ እንደሚኖረው የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሎፍቲ ቤንቼክሮን ተናግረዋል።

morocco.jpg

ከዚህ በተጨማሪም በውስጡ የፎቶ እና የተለያዩ የምስል ጋለሪዎች፣ ሬስቶራንት ሹቆች፣ ካፌ እና መጻህፍት መደብሮችን ያካትታል ነው ያሉት።

የትያትር ቤቱ ዲዛይን የተሰራው በትውልደ ኢራቃዊቷ የብሪታኒያ ዜጋ ዛሃ ሃዲድ ሲሆን፥ የትያትር ቤቱ ግንባታ አሁን 40 በመቶ ደርሷል።

ይህ የሁለገብ ትያትር ቤት በንጉስ ሞሃመድ ስድስተኛ በፈረንጆቹ 2006 ጥር ወር ይፋ የሆነው የቦሬግሬግ ሸለቆ ልማት ፕሮጀክት አካል ነው።

የልማት ፕሮጀክቱ በ6 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚከናወን ሲሆን፥ የራባት ግዙፉ ትያትር ቤት፣ የቅርስ አገልግሎት፣ የቅሪተ አካል ሙዚየም እና የሙዚቃ እና ሌሎች የኪነጥበብ ዘውጎች መከወኛ መድረኮች፣ የውሃ መዋኛ ገንዳ እና መናፈሻዎችን ያቀፈ መሆኑ ተነግሯልል፡፡

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፡-ሲ ጅ ቲ ኤን