የ6 ዓመቱ ጃፓናዊ በእድሜ ትንሹ ዲጄ በሚል በዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሰፈረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የስድስት ዓመቱ ጃፓናዊ በእድሜ ትንሹ የሙዚቃ አጫዋች(ዲጄ) በሚል ስሙ በዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሰፈረ፡፡

ታዳጊው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን እየጀመረ ቢሆንም፥ ሙዚቃ በማጫወት ክህሎቱና ብቃቱ ገና በህጻንነት እድሜው የዓለም ክብረወሰንን ለመያዝ በቅቷል፡፡

 

የታዳጊው ስም ኢትሱኪ ሞሪታ ይሰኛል፤ በስድስት ዓመት ከ114 ቀናት እድሜውም በዓለማችን በእድሜ ትንሹ የክለብ ሙዚቃ አጫዋች(ዲጄ) ተብሏል፡፡

Youngest-club-DJ.jpg

ታዳጊው በፒኦኔር ኤክስ ዲ ጄ ኤሮ የሙዚቃ ማጫወቻ በርካታ ሙዚቃዎችን እየመረጠ ታደሚዎች በተገኙበት ስፍራ ተጫውቷል፡፡

ከዚህ በፊትም በየክለቡ እየሄደ ሙዚቃ የማጫወት ልምድ እንዳለው እናቱ ተናግረዋል፡፡

Youngest-DJ-header.jpg

ታዳጊው መቼ ዲጄ የመሆን ፍላጎት እንዳደረበት ሲጠየቅ፥ "ሙዚቃ የሚያጫውቱ ሰዎችን እንዳየሁ ስራው የሚያስደስት ሆኖ በማግኘቴ ስራውን ጀመርኩ" ነው ያለው፡፡

ኢትሱኪ የሮክ ሙዚቃዎችንም መጫወት ይወዳል፡፡

በዓለም ትንሹ የክለብ የሙዚቃ አጫዋች በሚል በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ በመስፈሩ ምን እንደተሰማው የተጠየቀው ታዳጊው በጣም ደስ ብሎኛል፣ ዲጄ በመሆኔም ደስ ብሎኛል ነው ያለው፡፡

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፡-guinnessworldrecords