በለንደን የሚገኝ የግል ትምህርት ቤት ወንድ ተማሪዎች ቀሚስ እንዲለብሱ ሊፈቅድ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በእንግሊዝ ሰሜን ለንደን የሚገኝ አንድ የግል ትምህርት ቤት ወንድ ተማሪዎች ቀሚስ እንዲለብሱ ሊፈቅድ መሆኑ ተሰምቷል።

ሀይጌት የተባለው ይህ ትምህርት ቤት ለተማሪዎቹ የተለያዩ ቀለማት ስብጥር የሆነ የደንብ ልብስ እንዲለብሱ የሚያደርግ ሲሆን፥ ሆኖም ግን ስለ ጾታ የሚጠይቁ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል ሲሉ የትምህርት ቤቱ መምህራን ይናገራሉ።

ትምህርት ቤቱ ለሁሉም ክፍት የሆነ መጸዳጃ ቤት የከፈተ ሲሆን፥ ሁሉንም አይነት የስፖርት አይነቶችም ወንድ ሴት ሳይባል እኩል እንዲጫወቱም ይፈቅዳል።

በትምህረት ቤቱ የሚማሩ ሴቶች ከወንዶች ጋር ተመሳሳይ የሆነ ጃኬት፣ ሱሪ፣ ሸሚዝ መልበስ እና ከረቫት ማሰር ይፈቀድላቸዋል።

ሆኖም ግን ወንድ ተማሪዎች እንደ ሴቶች ቀሚስ መልበስ ቢፈልጉ እንኳ አይፈቀድላቸው፤ አዲስ እየተዛጋጀ ባለው የአለባበስ ስነ ስርአት ግን ወንዶችም ከሴቶች ደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቀሚስ መልበስ እንዲችሉ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

የትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር አዳም ፔቲት፥ አሁን ላይ ተማሪዎቹን የነድንብ ልቦሶቹ ቁጥር አንድ እና ሁለት የሚል መጠሪያ ይሰጠው የሚል ጥቄ እየጠየቅናቸው ነው ብለዋል።

የተማሪዎቹን የደንብ ልብስ የማመሳሰል ሀሳብ የመጣውም በትምህርት ቤቱ ከሚገኙ ተማሪዎች ጋር ጥያቄ እና መልስ በሚደረግበት ጊዜ እንደመጣም ርእሰ መምህሩ ተናግረዋል።

ከዚያን ጊዜ አንስቶም የተማሪዎቹን የደንብ ልብስ በምን መልኩ ማመሳሰል አለብን የሚለው ላይ እየሰራን ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ