1 ሜትር ከ20 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ድመት በቁመቱ ክብረወሰን ሊይዝ ይችላል ተብሏል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በአውስትራሊያ የሚገኘው እና 1 ሜትር ከ20 ሴንቲ ሜትር ገደማ ቁመት ያለው ድመት የዓለማችን ረጅሙ ድመት ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል።

“ኦማር” የተባለው ድመቱ በአውስትራሊያ ሜልበርን እንደሚገኝም ተነግሯል።

ድመቱ በአሁኑ ጊዜ በኢንስታግራም ላይ መነጋገሪያ መሆን የቻለ ሲሆን፥ የዓለም የድንቃድንቅ መዝገብም የድመቱን ባለቤት በማግኘት የድመቱን ቁመት በክብረ ወሰንነት እንደሚያሰፍረውም እየተጠበቀ ነው።

omar_2.jpg

ኦማር 14 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን፥ አሁን በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ክብረወሰን በመያዝ ከተመዘገበው ድመት በ2 ነጥብ 5 ሴንቲ ሜትር እንደሚበልጥም ተነግሯል።

በአሁኑ ጊዜ የዓለማችን ረጅሙ ድመት በሚል የተመዘገበው ሉዶ የተባለ ድመት ሲሆን፥ ቁመቱም 1 ሜትር ከ18 ሴንቲሜትር ገደማ እንደሆነ ተነግሯል።

ምንጭ፦ www.upi.com/Odd