በየቀኑ 60 ሺህ ንቦችን በፊቱ ላይ አስፍሮ ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሰው ወጣት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ህንዳዊው የ21 ዓመት የተፈጥሮ አድናቂ ወጣት 60 ሺህ ንቦች በመላ ፊቱ ላይ እንዲሰፍሩ አድርጎ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስን የዘወትር ተግባሩ አድርጎታል፡፡

በቅፅል ስሙ “ኔቸር ኤም ኤስ” የሚባለው ይህ ወጣት ንቦቹ ከቀፏቸው ይልቅ የእርሱን የፊት ቆዳ ለኑሮ ምቹ ሆኖ ስላገኙት በፊቱ ላይ ሲሰፍሩ ለማባረር የማይሞክር መሆኑን ገልፆ፥ ማንኛውንም እንቅስቃሴ ባደርግ ንቦቹ አይበሩም ብሏል፡፡

be_dance.jpg

አባቱ ሳጃኩማር በማር ምርት እና በንብ እንክብካቤ ተሸላሚ በመሆናቸው ልጃቸውም ህይወቱን በሙሉ ንቦች ባሉበት አካባቢ አድርጓል፡፡

“ኔቸር ኤም ኤስ” ንቦችን በፊቱ ላይ ለማስፈር ያልተለመዱ ተግባራትን ማከናወን የጀመረው ከአምስት ዓመት እድሜው ጀምሮ ነው፡፡

አሁን ላይ በቀፎ ውስጥ የነበሩት ንቦች በሙሉ በየቀኑ መኖሪያቸውን በኔቸር ኤም ኤስ የፊት አካል ላይ አድርገው ይውላሉ፡፡

beeeee.jpg

በህንድ ኬራላ አካባቢ የሚኖረውና የግብርና ተማሪው ይህ ወጣት ንቦች ፊቱን ሲነድፉት ምንም አይነት የህመም ወይም መጥፎ ስሜት እንደማይሰማው ተናግሯል።

“ንቦቹ ሲነድፉኝ እንዲያውም የጨዋታ ያህል የመቆንጠጥ ስሜት ነው የሚሰጠኝ” ብሏል፡፡

beee_read.jpg

“ኔቸር ኤም ኤስ” ቀኑን ሙሉ ንቦችን በፊቱ ላይ አስፍሮ ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳል፤ መፅሐፍ ያነባል፤ እንዲሁም ዳንስ ይደንሳል ተብሏል፡፡

 

 

 

 

 

ምንጭ፡- www.portsmouth.co.uk