አዲስ የተመረተች መኪናን ለ50 ሰዓታት የሳመችው ግለሰብ መኪናዋን ተሸልማለች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቴክሳስ ኦውስቲን ነዋሪዋ ዲሊኒ ጃያሱሪያ ኬ.አይ.ኤ ኦፕቲማ ኤል ኤክስ የተሰኘች አዲስ መኪናን ለመሸለም 50 ሰዓታት መኪናዋን የመሳም ውድድር ከ20 ተወዳዳሪዎች ጋር ተፎካክራለች፡፡

ሰኞ እለት ጧት አዲሷን ተሸከርካሪ ለማሸነፍ በተዘጋጀው የመሳም ውድድር ጃያሱሪያ ከሌሎች 20 ተወዳዳሪዎች ጋር በመሆን መኪናዋን መሳም ጀመረች፡፡

ህጉም ቀጥታ ከንፈርን ያለዕረፍት መኪናዋን ለ50 ሰዓት መሳም ሲሆን፥ ለ50 ሰዓት ያለድካም ያጠናቀቀ ሰው ውዷ ተሸከርካ እንደምትበረከትለት የውድድሩ ህግ ይደነግጋል፡፡

50ውን ሰዓት ሙሉ ብዙ ሰዎች ካጠናቀቁ አሸናፊው በዕጣ ይለያል፡፡

ተወዳዳሪዎቹ በመኪና መሳም ሂደቱ ውስጥ በየሰዓቱ የ10 ደቂቃ እረፍት አላቸው፡፡

Kiss-1.jpg

በዚህ 10 ደቂቃም ሰውነታቸውን መታጠብ ዘና ማድረግ እና ድካምን ለማስለቀቅ ይሞክራሉ፤ 10 ደቂው እንዳለቀም በከንፈራቸው መኪናዋን ግጥም አድርገው መሳም ይጠበቅባቸዋል፡፡

ይህን ካላደረጉ ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡

ሰኞ ምሽት ላይም አምስት ተወዳዳሪዎች መኪናዋን ያለማቋረጥ ባለመሳማቸው ከውድድሩ እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡

ማክሰኞ ምሽትም ተሸርካሪዋን ለመሳም ብርታት ያጡ 11 ሰዎች ከውድድሩ ተሰናብተዋል፡፡

የ21 ዓመቱ አሊሲያ ጂያንጂያኮሞ አፌ ውሃ መቋጠር ሲጀምር መኪናዋን መሳም አልቻልኩም በመሆኑም ከውድድሩ ወጣሁ ብሏል፡፡

Kiss-2.jpg

ውድድሩን ለማጠናቀቅም ሰዓታት ሲቀሩ በውድድሩ ላይ የዘለቁት የመጨረሻዋ ሰዓት ላይ ለመድረስ በስማርት ስልካቸው ላይ ማተኮር፣ ሙዚቃ ማዳመጥ ጀመሩ፡፡

በውድድሩ መጨረሻ ላይ ሰባት ተወዳዳሪዎች 50 ሰዓታትን መኪናዋን በመሳም ያሳለፉና የመጨረሻዋ ሰዓት ላይ የደረሱ ሆነው ተገኙ፡፡

በዚህም መሰረት ከሰባቱ መኪናዋን ማን እንደሚሸለም ዕጣ ወጣ፡፡

በዕጣው መሰረትም ኬ አይ ኦቲማ ኤል ኤክስ ተሸላሚ የ30 ዓመቷ ዲሊኒ ጃያሱሪያ ሆናለች፡፡

መኪናን ለረጅም ሰዓታት የመሳም ውድድርን ቻይና ከ2007 ጀምሮ እያካሄደች ሲሆን፥ የማሻብል ዘገባ እንደሚያሳየው በፈረንጆች 2017 የመኪና መመሳም ውድድር አዘጋጆች ተወዳዳሪዎች ለ70 ሰዓታት መኪና እንዲስሙ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ ኦዲቲ ሴንትራል

በምህረት አንዱዓለም