500 ኪሎ ግራም የምትመዝነዋ ግብፃዊት የክብደቷ ግማች በቀዶ ህክምና ተቀነሰላት

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 500 ኪሎ ግራም የምትመዝነዋ እና የዓለማችን ወፍራሟ ሴት የሚል መጠሪያ የተሰጣት ግብፃዊት ከክብደቷ ላይ ግማሽ ያክሉ መቀነሱ ተነግሯል።

ኤማን አባድ ኤል አትይ የምትባለዋ ይህች ግብፃዊት በህንድ የቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገላት ሲሆን፥ በአሁኑ ጊዜም ክብደቷ 250 ኪሎ ግራም እንደሆነ ተነግሯል።

ቤተሰቦቿ እንደሚናገሩት ኤማን ከቀዶ ህክምና በፊት 500 ኪሎ ግራም ገደማ ትመዝን ነበር፤ በዚህ የተነሳም ለ25 ዓመታት ከቤት ወጥቷ አታውቅም።

አሁን ላይ ግን ወደ ህንድ ተወስዳ ከሁለት ወር በፊት በተደረገላት ቀዶ ህክምና ክብደቷ በግማሽ መቀነስ መቻሉን ነው የሚናገሩት።

እንደ ሆስፒታሉ ገለፃ ኤማ አሁን በቀላሉ ዊልቼር ወንበር ላይ መቀመጥ የምትችል ሲሆን፥ ለረጅም ሰዓት ተቀምጣ መቆየትም ትችላልች።

የኤማ የሰውነት ክብደት መጠን በግማሽ መቀነስን ተከትሎም ሆስፒታሉ አዳዲስ ፎቶ ግራፎችን በኢንተርኔት ላይ አጋርቷል።

በሆስፒታሉ ኤማን በመከታተል ላይ የሚገኙት ዶክተር ላክዳላዋ፥ ለኤማ የተደረገላት የቀዶ ህክምና “ባሪያትሪክ” ወይም በተለምዶ የሰውነት ክብደት ቅነሳ ቀዶ ህክምና ነው የሚባል ነው ብለዋል።

እንዲህ አይነቱ የቀዶ ህክምና “የቦዲ ማክስ ኢንዴክሳቸው” 40 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ አሊያም 35 ሆኖ ከሰውነት ውፍረት ጋር የተያያዘ ሌላ የጤና እክል ላለባቸው ነው የሚደረገው።

እንደ ዶክተር ላክዳላዋ፥ “ኤማን በተከታታይና በፍጥነት የሰውነት ክብደቷ በመቀነስ ላይ ይገኛል፤ ሆኖም ግን በልጅነቷ ያጋጠማት የስትሮክ በሽታ የሰውነት ክፍሏን በአንድ በኩል ፓራላይዝ አድርጓል እንዲሁም ከመናገርና ምግብ ከመዋጥ ጋርም ችግሮች ይስተዋሉባታል” ብለዋል።

ሆስፒታሉ አሁን ላይ ኤማን በበቂ ሁኔታ የሰውነቷ መጠን እንዲቀንስ በመጠባበቅ ላይ ሲሆን፥ ክብዷታ እንደቀነሰም የሲቲ ስካን ምርመራ በማድረግ ለስትሮክ እንድታለጥ ያደረጋትን መንስኤ እንደሚለዩ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ