በርካታ ጥቅል የገንዘብ ኖት በናይጀሪያ ካዱና አውሮፕላን ማረፊያ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በናይጀሪያ የካዱና አውሮፕላን ማረፊያ በርካታ ጥቅል የገንዘብ ኖትወደ ሌላ ሀገር ሊዛወር ሲል ተይዟል፡፡

የተያዘው የገንዘብ መጠንም 155 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ነው ተብሏል፡፡

ገንዘቡ ናይራ የሚባለው የናይጀሪያ መገበያያ ሲሆን በአውሮፕላኑ ማረፊያ የፍተሻ ክፍል ሲደርስ ተይዟል፡፡

የናይጀሪያ የኢኮኖሚያዊ እና የፋይናንስ ወንጀሎች ኮሚሽን ቃል አቀባይ ኢብራሂም ባፓ እንዳሉት የገንዘቡ ምንጭ ከየት እንደሆነ እየተጣራ ነው፡፡

የኮሚሽኑ የወንጀል ክትትል ቡድን በካዱና አውሮፕላን ማረፊያ የያዘው ገንዘብ፥ 49 ሚሊየን ናይራ ሲሆን በአምስት ጥቁር ቀለም ያላቸው ጆንያዎች ውስጥ ነው የተገኘው፡፡

naigeriaa.jpg

በህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩ የተሳተፉትን አጣርቶ ለመያዝም ከፍተኛ የክትትል ሥራ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንት ሙሃመዱ ቡሃሪ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት በናይጀሪያ ያለውን የከፋ ሙስና መዋጋት ዋነኛ ሥራቸው እንደሚሆን ቃል ገብተው ነበር፡፡

 

 

 


ምንጭ፡-ቢቢሲ