በበረራ ወቅት ተኝታ የነበረቺው ተጓዥ የጆሮ ማዳመጫዋ በፈጠረው ፍንዳታ ነቃች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፕላን በረራ ወቅት የጆሮ ማዳመጫ ፈንድቶ በተጠቃሚዋ ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

ግለሰቧ ከቤጂንግ ወደ ሜልቦርን በመብረር ላይ በነበረው አውሮፕላን ሰትጓዝ መዚቀዘ እያዳመጠች ተኝታ ነበር፡፡

ሆኖም የጆሮ ማዳመጫዋ ሲፈነዳ ነቅታለች፡፡

በፍንዳታውም የጆሮ ማዳመጫ ገመዱ የነደደ ሲሆን የተፈጠረው ቃጠሎም ፊቷ እንዲጠቁርና እጇ ውሃ እንዲቋጥር አድርጓል፡፡

ስሟ ያልተጠቀሰቺው ግለሰቧ ስለሁኔታው ስትገልፅ ፍንዳታው ሲከሰት በጆሮ ማዳመጫዋ ሙዚቃ ስታዳምጥ እንደነበር ለአውስትራሊያ የትራንስፖርት ደህንነት ቢሮ ተናግራልች፡፡

የጆሮ ማዳመጫው ሲፈነዳ በሰውነቷ ላይ የመቃጠል ስሜት እንደተፈጠረባት፣ ፊቷም በጥቁር ብናኝ እንደለበሰ እና ከፊቷ ላይ ብናኙን ለማስወገድ እንደሞከረች ነው የገለፀቺው፡፡

headphones_2.jpg

የማዳመጫው ገመዶችም ተቆራርጠው የተወሰነ እሳት መፍጠራቸውን ጠቅሳለች፡፡

የበረራ ሰራተኞችም ተጎጂዋን ለመርዳት እሳት በፈጠሩ ገመዶች ላይ ውሃ በመርጨት አጥፍተውላታል፡፡

ሌሎቹ ተጓዦችም የጆሮ ማዳመጫው እና ባትሪው ሲቀልጡ በፈጠሩት መጥፎ ጠረን መታወካቸው ተነግሯል፡፡

የጆሮ ማዳመጫው የማን ኩባንያ ምርት እንደሆነ ባይጠቀስም ለፍንዳታው መፈጠር ምክንያት የሊትየም አዮን የሚጠቀም ባትሪ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የአውስትራሊያ የትራንስፖርት ደህንነት ቢሮም በአውሮፕላን የሚጓዙ ሰዎች የጆሮ ማዳመጫዎቻቸውን በአግባቡ እና በጥንቃቄ በመጠቀም ከመሰል አደጋ ሊቆጠቡ ይገባል ነው ያለው፡፡

በተለይም ሊቲየም አዮን የሚበዛባቸው ባትሪን የሚጠቀሙ ከሆነ መዘናጋት እንደሌለባቸውም አሳስቧል፡፡

 

 

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ