በስፔን የ64 ዓመቷ አዛውንት መንታ ልጆችን ወለዱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በሰሜናዊ ስፔን ቡርጎስ ከተማ ውስጥ የ64 ዓመቷ አዛውንት መንታ ልጆችን መውለዳቸው ተነገረ፡፡

አዛውንቷ መንታዎቹን የወለዱት በተደረገላቸው ዘመናዊ ህክምና መንገድ ነው ተብሏል፡፡

በእርጅና ጊዜ ለማርገዝ የሚያስችል ሳይንሳዊ መንገድ እንደተጠቀሙም ነው የተገለጸው፡፡

አዛውንቷ ወልደው የሳሟቸው መንታዎች ወንድ እና ሴት መሆናቸውም ተነግሯል፡፡

ወንዱ 2 ነጥብ 43 ኪሎግራም፣ ሴቷ ደግሞ 2 ነጥብ 2 ኪሎግራም ክብደት እንዳላቸው ተጠቁሟል፡፡

ልጆች እና ወላጅ አዛውንቷ በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸውን ሆስፒታሉ ጠቅሷል፡፡

ከቅርብ ጊዜ በፊት ሁለት ስፔናዊ እናቶች ከ60 ዓመታቸው በላይ በመውለድ የዜና ርዕስ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ