ከውሃ ፏፏቴነት ወደ “እሳት ፏፏቴነት” በካሊፎርኒያ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በካሊፎርኒያ በሚገኘው ዮሰሚት ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ በፀሐይ ብርሃን አማካይነት የሚፈጠረው “የእሳት ፏፏቴ” የበርካቶችን ቀልብ ስቧል።

የዮሰሚት ብሔራዊ ፓርክ በየካቲት ወር ከሚያጋጥሙት ግሩም የተፈጥሮ ክስተቶች ውስጥ አንዱ የፈረስ ጭራ በሚመስል ሁኔታ ቁልቁል የሚምዘገዘገው የእሳት ፏፏቴ ነው።

የውሃ ፏፏቴን ማየት የለመደ ሰው ይህን የእሳት ፏፏቴ ሲመለከት፥ አግራሞቱ እንደሚገዝፍ እና "እንዴት ሊሆን ቻለ?" የሚል ጥያቄ እንደሚያነሳ ይጠበቃል።

yosemite1.jpg

ታዲያ ይህ ብርቱካናማው እና የቀለጠ አለት የሚመስለው ፏፏቴ የሚከሰተው፥ የፀሐይ ጨረር በተወሰነ ማዕዘናዊ አቅጣጫ በውሃ ፏፏቴው ላይ በቀጥታ በሚያርፍበት ጊዜ ነው።

ይህ ተፈጥሯዊ ገፅታ እውነት የማይመስል ደማቅ ብርቱካናማ ቀለም ያለው ሲሆን፥ ከገደሉ አፋፍ ቁልቁል ሲምዘገዘግ የእሳተ ገሞራ ቅልጥ ድንጋይ ወይም የእሳት ፏፏቴ እንጅ ተፈጥሯዊ ውሃ አይመስልም።

yosmite.jpg

ይህ አስገራሚ የተፈጥሮ መልክ፥ በየካቲት ወር ለሁለት ሳምንታት ብቻ የሚከሰት እንደሆነም ተነግሯል።

ታዲያ በየካቲት ወር በርካታ ጎብኝዎች ማታ ማታ ትዕይንቱን ለማየት በስፍራው እንደሚታደሙም ተጠቁሟል።

yosemite2.jpg

የፓርኩ ሃላፊ ስኮት ጌዲማን እንዳሉት፥ “የእሳት ፏፏቴ”ን ለማየት የሚመጡ ጎብኚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።

 

 

ምንጭ፡-ሲኤንኤን

በምህረት አንዱዓለም

android_ads__.jpg