አርጀንቲናዊቷ አዛውንት የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች የመሆን ህልማቸውን በ83 ዓመታቸው አሳክተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አርጀንቲናዊቷ አዛውንት ከልጅነታቸው ጀምሮ ሲያልሙት የነበረውን የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች የመሆን ህልም በ83 ዓመታቸው ማሳካታቸው ተነግሯል።

አዛውንቷ ዓና ኦባሪዮ ፔሬይራ ይባላሉ፥ ከልጅንታቸው አንስተው ለሜዳ ቴኒስ ልዩ ፍቅር እንዳላቸው እና በዚህም ስኬት ላይ መድረስ ይፈልጉ እንደነበር ይናገራሉ።

ሆኖም ግን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ1949 ላይ ቴኒስ መጫወት ማቆማቸውን የሚናገሩት ኦባሪዮ፥ ምክንያቱ ደግሞ የባለቤታቸው ክልከላ ነበር ይናሉ።

ከዚያን ጊዜ አንስቶም ለቀጣይ 20 ዓመታት የወለዷቸውን 20 ልጆች ማሳደግን ስራቸው እንደሆነም ነው ኦባሪዮ የሚናገሩት።

አሁን ላይ ግን አና በ83 ዓመታቸው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች የመሆን ህልማቸውን እንዳሳኩ ተናግረዋል።

የባለቤታቸውን ሞት ተከትሎ የሜዳ ቴኒስ ልምምዳቸውን በ60 ዓመታቸው አሀዱ ብለው እንደ አዲስ የጀመሩት ኦባሪዮ፥ በሳምንት ለሶስት ቀናት ልምምድ እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።

“መወዳደር እወዳለው፤ ማሸነፍ እወዳለው” የሚሉት ፥ ለዚህም በርትተው እንደሚሰሩ ነው የሚናገሩት።

በሀገራቸው አርጀንቲና እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ በሆነ ዘርፍ ላይ ገብተው የተወዳደሩት አና አጠቃላይ ጥሩ ውጤት ማስመዝገባቸውም ተነግሯል።

ውድድሩን በሚያደርጉበት ጊዜም ሁለት ልጆቻቸው እና ስድስት የልጅ ልጆቻቸው በስፍራው ተገኝተው ተመልክተዋል።

ኦባሪዮ ከእድሜ እኩዮቻቸው ጋር ሲነጻጸሩም በሜዳ ቴኒስ ዘርፍ በሀገሪቱ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በፈረንጆቹ 2017 በአሜሪካ ፍሎሪዳ በሚደረገውየሜዳ ቴኒስ ውድድር ላይ እንደሚካፈሉ ያስታወቁት አዛውቷ፥ ውድድሩን በአንደኝነት ለማጠናቀቅ ተዘጋጅቻለው ብለዋል።

አና ኦባሪዮ ፔሬይራ 37 የልጅ ልጆች ያሏቸው ሲሆን፥ የልጅ ልጃቸው የሆነችው የ19 ዓመቷ ሉፔ “በጣም ጥሩ እና ነፃ የሆነ የተነሳሽነት ስሜት አላት” ብላለች።

“በጣም ለየት ያለች አያት አለችኝ” ስትልም ተናግራለች።

ምንጭ፦ www.emirates247.com

android_ads__.jpg