ለ75 አመታት ዮጋ ያስተማሩት የ98 አመት አዛውንት የህይወት ፍልስፍናቸውን ይናገራሉ..

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታኦ ፖርቾን ላይንች ይሰኛሉ፤ የ98 አመት አዛውንት ናቸው።

ባለፉት 75 አመታትም ሁል ጊዜ በማለዳ የሚያከናውኑት አንድ የተለመደ ተግባር አላቸው፤ ከ11 ስአት ጀምሮ ለተማሪዎቻቸው የዮጋ ትምህርት መስጠት።

የአለማችን የእድሜ ባለፀጋ የዮጋ አስተማሪ ናቸው የተባለላቸው ፖርቸን ላይንች በህንድ አድገው በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ኒውዮርክ ነው የሚኖሩት።

ፖርቸን ላይንች ከሌላኛዋ የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ ዶክተር ቴሪ ኬነዲ ጋር በመሆን አንድ አነቃቂ ቪዲዮ ለእይታ አቅርበዋል።

yoga1.jpg

“ይቻላል፤ የማይቻል ነገር ምንም የለም” ይላሉ ፖርቸን ላይንች።

“ሁል ጊዜም ከእንቅልፍዎ ሲነቁ ለውስጣችሁ ዛሬ የእኔ ነው፤ ደስ የሚል ቀን ይሆናል” የማለት ልምድ ይኖራችሁም ይላሉ።

ፖርቸን ላይንች የ8 አመት ታዳጊ እያሉ ዮጋ ለመስራት ቢፈልጉም “ዮጋ የሴቶች” አይደለም የሚል አስተሳሰብ እንደነበር ያስታውሳሉ።

ይሁን እንጂ ፍላጎታቸው ከፍ ያለ ስለነበር የዮጋ አሰልጣኙን አሳምነው ከእኩያዎቻቸው ወንዶች ጋር ስልጠናውን ይጀምራሉ።

ውስጣዊ ስሜታቸው ለዮጋ የተፈጠርሽ ነሽ የሚላቸው ፖርቸን ላይንች አዕምሯቸው በመራቸው መንገድ ተጉዘው ባለፉት 75 አመታት ዮጋ አሰልጥነዋል።

ዶክተር ኬነዲም ፖርቸን ላይንች መነቃቃት ፈጥረውብኛል ይላሉ።

ስለ ዮጋ ግንዛቤ ለመፍጠር ከፖርቸን ላይንች ጋር አለምን አብረን ዞረናል ያሉት ዶክተር ኬነዲ፥ ብዙ ሰዎችም ሁለታችን ስንጣመር የበለጠ ውጤታማ እንደምንሆን ይነግሩናል ብለዋል።

ውስጣችን ካዳመጥነው የመኖራችን ትርጉም እንረዳለን የሚሉት ፖርቸን ላይንች፥ በወጣትነታቸው ከዮጋ አስተማሪነታቸው ባሻገር የፋሽን ሞዴል ነበሩ።

በ1951 በወጣው Show Boat እና በ1954ቱ The Last Time I saw Paris ፊልም ላይ ኤልሳቤጥ ቴይለርን ወክለው ተውነዋል።

ባለቤታቸው ቢል ላይንችም ባህላዊው የተመስጦ ልማድ የ98 አመቷን አዛውንት ሰውነት የወጣት ቁመና እንዲላበስ ከማድረግ ባለፈ አዕምሮዋን እና መንፈሷን አነቃቅቶታል ብለዋል።

“በየቀኑ ወጣትነት እና ጥንካሬ ይሰማኛል” የሚሉት ታኦ ፖርቸን ላይንች፥ የረጅም እድሜያቸው ሚስጢር አትክልት ተመጋቢነታቸው እና የዮጋ ስፖርት መሆኑን ያነሳሉ።

አንዳንድ ጊዜ ወይን መቅመሳቸው እና ቼኮሌት መመከባቸውም የራሱ አስተዋፅኦ እንዳለው በቪዲዮ መልዕክታቸው ላይ ተናግረዋል።

አዛውንቷ ታኦ ፖርቸን ላይንች ከሁለት አመት በፊት በአሜሪካ የተሰጥኦ ውድድር ላይ ቀርበው በ96 አመታቸው ያሳዩትን ዳንስ ይመልከቱ

 

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk/

 

 


በፋሲካው ታደሰ

 

android_ads__.jpg