የ105 ዓመቱ ብስክሌተኛ በሰዓት 22 ኪሎ ሜትር በመንዳት አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግበዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ105 ዓመት አዛውንት የሆኑት ፈረንሳዊ በስክሌተኛ በሰዓት 22 ኪሎ ሜትር በመንዳት አዲስ የዓለም ክብረወሰን በእጃቸው ማስገባታቸው ተሰምቷል።

ሮበርት ማርቻርድ የተባሉት የስብክሌት ስፖርተኛው ሳይክሉን በትራክ ላይ ያሽከረከሩ ሲሆን፥ በአንድ ሰዓት ውስጥ በአጠቃላይ 92 ዙር መንዳታቸውም ታውቋል።

ማርቻርድ ክብረወሰኑን በሰበሩበት ጊዜ በርካታ ተመልካች ተገኝቶ እንደነበረም ተነግሯል።

አዛውንቱ ብስክሌተኛ ከብረወሰኑን መያዛቸውን ተከትሎ በሰጡት አስተያየት፥ ከዚህ በላይ በመብረር ክብረወሰኑን መያዝ እችል ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

“10 ደቂቃ ቀርቶ ማስጠንቀቂያ ሲሰጠኝ አላየውም ነበር፤ ያኔ ማስተዋል ብችል ኖሮ ፍጥነቴን ከዚህ በላይ በመጨመር የተሻለ ርቀት በመጓዝ ክብረ ወሰኑን መያዝ እችል ነበር” ብለዋል።

አሁንም ቢሆን ይህን ክበረ ወሰን የሚጋራኝን ተፎካካሪ እየጠበኩ ነው፤ ከተገኘ ከዚህ በበለጠ ርቀት ክብረወሰኑን የግሌ ለማድረግ ሙሉ አቅም አለኝ ሲሉም ተናግረዋል።

ማርቻርድ ከዚህ ቀደም ከ100 በላይ የብስክሌት ስፖርት ዘርፍ ክብረ ወሰኖችን በእጃቸው ላይ ማስገባት መቻላቸውም ተነግሯል።

“ሁሌም አዳዲስ ነገሮችን ማሳካት የህይወታቸው አንድ አካል ነው” ያለው የማርቻርድ አሰልጣኝ ጄራርድ ሚስትለር፥ “የያዙትን ክብረወሰን ማሻሻል አንደፈገሉ ከነገሩኝ በቃ ይሳካል፤ ማርቻርድ ለሁላችንም ትልቅ ትምህረት የሚሆኑን ናቸው” ብለዋል።

ምንጭ፦ www.upi.com/Odd

android_ads__.jpg