የቴሌቪዥን ሪሞት የሰረቀው ግለሰብ የ22 ዓመት የእስር ቅጣት ተላልፎበታል

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ ቺካጎ ኢሊኒዮስ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ የቴሌቪዥን የርቀት መቆጣጠሪያ (ሪሞት ኮንትሮለር) በመስረቁ ምክንያት የ22 ዓመት የእስር ቅጣት ተላልፎበታል።

ኤሪክ ብራምዌል የተባለው ይህ ግለሰብ እድሜው 35 ዓመት ሲሆን፥ ዩኒቨርሳል የሆነ የቴሌቪዥን የርቀት መቆጣጠሪያ (ሪሞት ኮንትሮል) ተመሳሳይ ከሆነ የመኖሪያ አፓርትመንት አካባቢ ሰርቀሃል በሚል ከስ ነው ፍርድ ቤት የቀረበው።

እንደ ቺካጎ ትሪቢዩን ዘገባ ብራምዌል ከዚህ ቀደምም የቴሌቭዥን የርቀት መቆጣጠሪያ (ሪሞት ኮንትሮል) እና የቴሌቭዥን ስርቆት ላይ ተሳትፎ እንደነበረው ያሳያል።

ሆኖም ግን ብራምዌል ለመጨረሻ ጊዜ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2015 የፈፀመው የቴሌቭዥን ሪሞት ስርቆት ጠበቆች ጠንከር ያለ ክስ እንዲመሰርቱበት ምክንያት ሆኗል።

ይህንን ተከትሎ ባሳለፍነው ሳምንት ፍርድ ቤት የቀረበው ብራምዌል የ22 ዓመት የእስር ቅጣቱን ተከናንቧል።

የቅጣት ውሳኔው በዝቷል የተባሉት ጠበቆች፥ ብራምዌል አሁን ከሰረቀው የቲቪ ሪሞት በላይ በርካታ ጊዜ ህግን ተላልፏል፤ ከዚህ ተግባሪ ይቆጠባል በሚል በርካታ ጊዜም ታልፏል፤ አሁን ግን የእጁን ነው ያገኘው ሲሉም ተናግረዋል።

የቴሌቪዥን ሪሞት የመስረቅ ሱስ የተጠናተው ብራምዌል እስር ቤት እያለም የእጅ ዓመሉ እንዳያስቸግራቸው ቴሌቪዥን ያለበት ቦታ ባይደርስ መልካም ነው ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።


ምንጭ፦ www.cnet.com

android_ads__.jpg