የዓለማችን ፈጣኑ ተንቀሳቃሽ አልጋ…

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለማችን ፈጣኑ ተንቀሳቃሽ አልጋ በእንግሊዝ ኩባንያዎች መሰራቱ ተሰምቷል።

አልጋው በሰዓት እስከ 135 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን፥ በሆቴል ዶት ኮም እና በእንግሊዙ የውድድር ተሽከርካሪ አምራች ትብብር መሰራቱም ተነግሯል።

አልጋውን የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ለማስመዝገብ በዱባይ ሙከራ ተደርጎበታል።

የውድድር ተሽከርካሪዎችን የሚነዳው ቶም ኦንስሎኮል አልጋውን በኢሚሬትS ሞተር ስፖርት ኮምፕሌክስ ወስጥ በሰዓት እስከ 135 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ፍጥነት አሽከርክሯል።

አልጋውን ያሽከረከረው ቶም፥ “ከሆቴልስ ዶት ኮም ጋር በመሆን የዓለም ፈጣኑ አልጋ ክብረ ወስንን ለመረከብ ሙከራዬን እድርጌያለው” ብሏል።

“ፈጣኑን አልጋ ማሽከርከር የማይረሳ ትውስታን የሚያጭር ነው፤ የዓለምን ክብረወሰን እንደምንይዝም ሙሉ እምነት አለኝ” ሲል ተናግሯል።

ሆቴልስ ዶት ኮም አልጋውን ያሰራው በመካከለኛው ምስራቅ ስራውን የጀመረ መሆኑን ለማብሰር እንደሆነም ተሰምቷል።

ከዚህ ቀደም ክብረ ወሰን በሰዓት 110 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ አልጋ ሲሆን፥ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2009 ነው የዓለም የክብረወሰኖች እና ድንቃድንቆች መዝገብ ላይ የሰፈረው።

ምንጭ፦ www.upi.com/Odd_News

android_ads__.jpg