ዘጠና እና መቶ ሃያ ደቂቃ (921)

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና የሚገኝ ሪል እስቴት ውስጥ የሽያጭ ባለሙያ የሆኑት ሰራተኞች የስራ አፈፃፀማቸውን ለማሻሻል አለቃቸው በጥፊ እድትመታቸው መማፀናቸው ተሰምቷል።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል በአንኮበር ወረዳ ጨፋ ቀበሌ አንድ ነብር መኖሪያ ቤት ገብቶ በአምስት ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡባዊ ፈረንሳይ ኢለኒ ከተማ የሚገኝ አንድ ቤተመዘክር ለበርካታ ዓመታት ይዟቸው ከቆየው 140 የስዕል ስራዎች 82 የሚሆኑት ሀሰተኛ ሆነው መገኘታቸው ተነገረ።


ካታስትሮፊ የተሰኘው ይህ ቤተመዘክር ኢትነኒ ተሩስ የተሰኘን ሰዓሊ ውጤት በመስብሰብ የሚታወቅ ነው።

በዚህም ቤተመዘክሩ ኢትነኒ ተሩስ የተባለውን  ታዋቂ ሰዓሊ ውጤቶች ከ20 ዓመታት በላይ በሰበሰበበት ወቅት 193 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንደወጣበት ተነግሯል።

ኤሪክ ፎርካዳ የተባለ የቤተመዘክሩ የበላይ ጠባቂ በአንድ ወቅት ቤተመዘክሩ በሚታደስበት ወቅት በውስጡ ያሉት ስዕሎች ሰዓሊው ህይወቱ ካለፈ በኋላ የተሰበሰቡ መሆናቸውን መመልከቱን ተናግሯል ።

ይህ አጋጣሚ የታሪክ ባለሙያዎች በተሩስ በቤተመዘክሩ በሚገኙት የስዕል ውጤቶች ላይ ምርመራ እንዲያደርጉ እንዳስገደዳቸው ታውቋል። 

“በአንዱ የስዕል ውጤት ላይ የእጅ ጓንቴ ሲያርፍ በስዕሉ ላይ የነበረው ፌርማ ጠፍ” ሲል የቤተመዘክሩ የበላይ ጠባቂ ፍራንኮ በወቅቱ ያጋጠመውን ጉዳይ ገልጿል።

ይህ ሀሰተኛ የስዕል ውጤት ተሩስ ይጠቀምበት ከነበረው የጥጥ እና የሸራ ውህደትጋር እንደማይመሳሰልም ባለሙያዎቹ አስታውቀዋል።

በዚህ መሰረት ሙያተኞች ባደረጉት የማጣራት ስራ በቤተመዘክሩ ከሚገኙት 140 የስዕል ውጤቶች መካከል ከ82 የማንያንሱት የስዕል ውጤቶች ሀሰተኛ ሆነው መገኘታቸው ተረጋግጧል።

ይህ ቤተመዘክር ካታላን በሚገኙ እና በተመሳሳይ እና ሀሰተኛ የስዕል ውጤቶች በሚያዘጋጁ አካላት ጥቃት እንደደረሰበት የታመነ ሲሆን ወንጀለኞቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ግፊት እየተደረገ ነው ተብሏል።

ኢትነኒ ተሩስ የተሰኘው ተመሳሳይ የስዕል ውጤት የተዘጋጀበት ሰዓሊ በፈረንጆቹ 1852 እንደተወለደ እና በ1992 ህይወቱ እንዳለፈ የህይወት ታሪኩ ያመለክታል።

ምንጭ፥ ኦዲቲ ሴንትራል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሜክሲኮ የ63 የህግ ታራሚ ጥንዶች የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን በእስር ላይ እያሉ በአንድ ስፍራ መፈፀማቸው ተነግሯል።