ዘጠና እና መቶ ሃያ ደቂቃ (1400)

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሮም ጆርጂያ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ ምንም እጣ የለውም ብሎ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ጥሎት ከነበረው የሎተሪ ትኬት 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ማሸነፍ ችሏል።

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 7 ፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ባለው አገር አቀፍ የዳያስፖራ ቀን ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መካከል ከ20 ዓመት በኋላ ከጀርመን ከተመለሱ ገና አንድ ዓመት የሆናቸው አቤልና ሰላም የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን የሚያመርትና ለኢንጀክሽን ማሽኖች የሞልዲንግ ስራን በዋናነት የሚሰጥ አገልግሎትን እያከናወኑ ነው።

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 6 ፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ36 ዓመቱ አሜሪካዊ ኒክ ዋሌንዳ ከ1 ሺህ 576 ጫማ ማለትም ከ480 ሜትር ከፍታ ላይ የተዘረጋ ቀጭን ገመድ ላይ ያለምንም የጥንቃቄ ገመድ እርዳታ በመሄድ  የአለማችን ረዥሙን እርምጃ አካሄደ።

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 6 ፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በስህተት ከማታውቀው ሰው የፌስቡክ ጓደኛ ሁኚኝ ጥያቄን በአዎንታ የተቀበለችው ግለሰብ ከእንግዳው ጋር በጋብቻ ተጣመረች።