የመድሃኒት ግዢ መዘርዝር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመድሃኒት እና የህክምና ግዢ መዘርዝር በዛሬው እለት ይፋ ተደርጓል።

የመድሃኒ ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ዛሬ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሒዷል።

ኤጀንሲው ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይም ለህክምና አገልግሎት የሚዉሉ ቁሳቁሶቹን እና ዋና ዋና መድሀኒቶች የግዠ መዘርዝር ይፋ አድርጓል ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይረክተር ዶክተር ሎኮ አብርሃም፥ የግዥ መዘርዝር መዘጋጀቱና ይፋ መሆኑ አስፈላጊ መድኃኒቶችና እና የህክምና ቁሳቁሶች በፋጥነት እና በፍትሀዊነት ተገዝተው ለጤና ተቋማት እንዲሰራጩ ለማድረግ ይረዳል ነው ያሉት።

ዶክተር ሎኮ በመድሐኒት አቅርቦት ላይ የሚስተዋለውን ክፍተት ለመሙላትም ኤጀንሲው ከጤና ተቋማት እና ከግሉ ዘርፍ ጋር አብረን እየሰራን ነው ብለዋል ።

በስላባት ማናዬ