የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ወንበር ማልበሻዎችና ውስጣዊ አከላን ለማምረት ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ወንበር ማልበሻዎችና ሌሎች ውስጣዊ አካላትን ለማምረት ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተገለጸ።

ምርቶቹን ለመጀመር ጥናቱን ያጠናቀቀው የአየር መንገዱ ወደ ምርት ለመሸጋገር ኤሲኤም ከተባለው የጀርመን ኤሮስፔስ ኩባንያ ጋር ስምምነት መርራረሙን ገልጿል።

የስምምነቱ አላምም የአውሮፕላን ወንበር ማልበሻ፣ የደህንነተ ቀበቶዎችን እና ሌሎች የአውሮፕላን ውስጣዊ ክፍሎችን በሀገር ውስጥ ለማምረት ነው ተብሏል።

ኩባንያው የዓለም አቀፉን አቪዎሽን መስፈርት ያሟሉ የአውሮፕላን ወንበር ማልበሻ፣ የደህንነተ ቀበቶዎችን እና ሌሎች የአውሮ ፕላን ውስጣዊ ክፍሎችን በአውሮፓ ገበያ በማቅረብ ታዋቂ መሆኑም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የአየር መንገድ ጥሬ እቃዎችን ከውጭ በማስገባት ምርቶችን ሀገር ውስጥ ለመጀመር እየሰራ ሲሆን፥ በቅርብ ጊዜ ለዚሁ ስራ ግባዓት የሚሆኑ ምርቶችን ከቆዳና ከጨርቃ ጨርቅ በሀገር ውስጥ በማምረት እውቅና ለማግኘት እንደሚሰራም ተጠቁሟል።

ዘርፉ የውጭ ምንዛሪ ከማስገኘቱም በላይ ለ100 ያህል ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠርም ያስችላል ተብሏል።