የሃምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ በሃምሌ ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በስተቀር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ብሏል።

በሃምሌ ወር የአውሮላን ነዳጅ ዋጋ በሰኔ ወር ሲሸጥበት ከነበረው በሊትር ብር 25 ብር ከ91 ሳንቲም፥ 1 ብር ከ25 ሳንቲም ቅናሽ በማድረግ 24 ብር ከ66 ሳንቲም ይሸጣል።

ሌሎች የነዳጅ ምርቶች በሰኔ ወር ሲሸጡበት በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥሉ የሚኒስቴሩ መግለጫ ያመላክታል።