የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ልማት ባንክ አዳዲስ ፕሬዚዳንቶች ተመደበላቸው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳዲስ ፕሬዚዳንቶች ተመደበላቸው።

የመንግስት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ለሁለቱ ባንኮች አዳዲስ ፕሬዚዳንቶች ተመድበዋል።

በዚህ መሰረት አቶ ባጫ ጊኒ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመድበዋል።

አቶ ባጫ ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው አገልግለዋል።

በሌላ በኩል አቶ ሃይለኢየሱስ በቀለ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳነት ሆነው ተመድበዋል።

አቶ ሃይለኢየሱስ የባንኩ ፕሬዚዳንት የነበሩትን አቶ ጌታሁን ናናን ተክተው ነው የተመደቡት።

አዲሱ የባንኩ ፕሬዚዳንት የቀድሞው ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ማገልገላቸው የሚታወስ ነው።