ለ5 ቀናት የሚቆይ ሀገር አቀፍ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ኢግዚቢሽንና ባዛር ሊካሄድ ነው

አዲስ አባበ፣ ሰኔ02፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለ5 ቀናት የሚቆይ ሀገር አቀፍ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ኢግዚቢሽንና ባዛር ሊከፈት መሆኑን የፌደራል አነስተኛና መካከለኛ ማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኤጀንሲ አስታውቋል።

ኤጀንሲው ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመላከተው ከፊታችን ሰኔ 5-10፣2010 ለ5 ቀናት የሚቆይ ሀገር አቀፍ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ኢግዚቢሽንና ባዛር ሊካሄድ ነው።

ከዘጠኙም ክልሎችና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የተዉጣጡ 201 የዘርፉ አምራቾችና ከ13 የተለያዩ የዉጭ ሀገራት የሚገቡ ኩባንያዎች በዚሁ ፕሮግራም ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም የኢፌዴሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዶ/ር አምባቸዉ መኮነን ገልጸዋል።

ከ20 ሺህ በላይ እንግዶች ኢግዚቢሽኑን እንደሚጎበኙትና ከ1ነጥብ8 ሚሊየን ብር በላይ የሽያጭና የገብያ ትስስር ይፈጠራል ተብሎ እንደሚጠበቅም በኤጀንሲው መግለጫ ተመላክቷል።

በዳዊት በሪሁን