የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጄኔቭ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ሰኔ፣ 1፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ100ኛ አውሮፕላኑ ወደ ጄኔቭ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጄኔቭ የሚያደርገው በረራ በአለም አቀፍ ደረጃ 110ኛ መዳረሻው ሲሆን፥ በአውሮፓ ያለውን መዳረሻ ደግሞ ወደ 12 እንደሚያሳድገው ተጠቁሟል።

አየር መንገዱ ወደ ጄኔቭ የሚያደርገው በረራም በሳምንት ሶስት ቀን መሆኑ ታውቋል።gg.jpg

አየር መንገዱ ወደ ጄኔቫ የጀመረው በረራ ከአፍሪካ የመጀመሪያ የ100 አውሮፕላኖች ባለቤት ባደረገው ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላን የሚደረግ ነው።

አዲስ አበባ እና ጄኔቫ የበርካታ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ተቋማት መቀመጫ በመሆናቸው የሁለቱን ከተሞች ግንኙነት ያጠናክረዋል ተብሏል።

ከዚህ በላፈ በሀገራቱ መካከል የንግድ ግንኙነት ለማሳድግ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።