የደቡብ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን 6 ነጥብ 15 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ

አዲስ አባባ፣ ግንቦት 6፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 6 ነጥብ 15 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ 10 ነጥብ 23 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ነበር፡፡

በዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ የዓመቱን 60 ነጥብ 13 በመቶ ማሳካት ችያለው ብሏል።

አፈጻጸሙም ከባለፈዉ ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ1 ነጥብ 42 ቢሊዮን ብር ብልጫ ማሳየቱን ገልጸዋል።

በየጊዜዉ የክልሉ ገቢ የመሰብሰብ አቅም እያደገ የመጣ ሲሆን፥ ከግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ጋር ተቀራርቦ መስራትና የታክስ ህጎች ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ለዉጤቱ አጋዥ ሆነዋል ተብሏል፡፡

አሁንም ቢሆን የሚታየዉ የግብር ስወራ፣ ማጭበርበረ እና ደረሰኝ ያለመቁረጥ የገቢ አሰባሰቡ ማነቆዎች መሆናቸውን የክልሉ ባለስልጣን የዕቅድ ዝግጅት ክትትል፣ ግምገማና ግብረመልስ ዳይሬክተር ገልጸዋል፡፡

 

በአዳነች አበበ